lørdag 16. februar 2013

የእነ አቶ አንዱአለም አራጌ ይግባኝ ተራዘመ


በፌደራሉ አቃቤ ህግ በሸባሪነት ክስ ተመስርቶባቸው በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸው የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አቶ አንዱዓለም አራጌ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን፣ አቶ አንዱዓለም አያሌው ፣ አቶ ክንፈሚካኤል ደበበ የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም 6 ኪሎ ለሚገኘው የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኛ በጠየቁት መሰረት ለየካቲት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ለውሳኔ ተቀጥሮ እንደነበር ይታወቃል።

ነገር ግን በዕለቱ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመሐል ዳኛው ሳይገኙ ከመቅረታቸውም በላይ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ውሳኔውን ለመስጠት ጉዳዩ ሰፋ ያለ ጊዜ ስለሚፈልግ አይተን አልጨረስንም የሚል መልስ ሰጥቷል፡፡

 በዚህም ምክንያት የይግባኙን የመጨረሻ ፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ለ3ኛ ጊዜ ለመጋቢት 18 ቀን 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar