onsdag 20. februar 2013

የተመራጭ እጩዎች ምዝገባ በተጠናቀቀ በሳምንቱ ዛሬም ምዝገባ እየተካሄደ ነው



በመጪው ሚያዚያ ለሚካሄደው የአዲስ አበባና አካባቢ ምርጫ፣ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ባለፈው ሳምንት የእጩዎች ምዝገባ መጠናቀቁን አውጆ ነበር። ኢሳት ባለው የመረጃ መረብ ለማረጋጋጥ እንደቻለው በቦረና ዞን ቡሌ ሆራ ወረዳ የተማራጮች ስም ዝርዝር አለመተላለፉን ምርጫ ቦርድ ለኢህአዴግ ከገለጸ በሁዋላ ከክልልና ከዞን የተውጣጡ የኢህአዴግ አመራሮች ወደ ወረዳው በመሄድ አቶ ሀይሌ አየለ የተባሉትን የኦህዴድ ኢህአዴግ የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ ከስልጣን ካባረሩት በሁዋላ ከትናንት ጀምሮ የተመራጮች ምዝገባ እንደአዲስ ተጀምሯል።

ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቁ በይፋ ከተገለጠ በሁዋላም እንዲሁ ምዝገባ እንዲካሄድ መፍቀዱን የተመዘገቡ ሰዎችን በማነጋገር መዘገባችን ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በመጪው ምርጫ ለመሳተፍ ያልፈቀዱ 33 የፖለቲካ ድርጅቶች 28ቱ ፓርቲዎች ኢህአዴግን በጋራ ለመታገል የሚያስችልን ህብረት ለመመስረት የመግባቢያ ስምምነት ለመፈራረም ወሰነዋል፡፡ ፓርቲዎች ረጅም ጊዜ የወሰደ ምክክር ካደረጉ በኋላ የካቲት 19 ቀን 2005 ዓ.ም የመግባቢያ ስምምነቱ ን ለመፈራረም መወሰናቸውን ዘጋቢያችን ገ_ልጸዋል፡፡ ፓርቲዎቹ በጋራ ለመስራት የጀመሩትን እንቅስቃሴ አጠናክረው በመቀጠል በቅርቡ ወደ ተሻለ የፓርቲ ስብስብ እንደሚያድጉ ገልጸዋል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar