onsdag 19. mars 2014

« የጣይቱ ልጆች» ከየካቲት 30 እስከ ዛሬ መጋቢት 9 የነበሩበት ሁኔታ

እመቤት ግርማ ( 18 አመት ወጣት)፣ ንግስት ወንዳፍራዉ፣ መታሰቢያ ስዩም፣ ወይንሸት ንጉሴ፣ ምኞት መኮንን በሩጫ ወቅት ሁከት ፈጥራችሁላ ተብለው ከታሰሩ «የጣይቱ ልጆች» መካከል የሚገኙ ናቸው።
የካቲት 30 2006 ዓ.ም 
እሑድ ቀን ነው። በተዘጋጀው የሴቶች የ500 ሩጫ በርካታዎች ይሮጣሉ። ቢጫ ኬኔቴራ ለብሰዋል። ሩጫዉ እንደተጀመረ ድምጾች መሰማት ጀመሩ። የስድብ፣ የክፉ አይደለም። «የጣይቱ ልጆችን ነን፤ የሚኒሊክ ልጆች ነን፣ ለነጻነት ነው የምንሮጠዉ፣ እርቦናል፣ መብታችን ይከበር፣ የታስሩ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ …» የሚሉ ድምጾች። በሌሎች ሯጮች ላይ ጠጠር አልተወረወረም። የወደመ ንብረት የለም። መንገዶች አልተዘጉም። ሩጫዉ አልተስተጓጎለም። በሰላም ተጀመሮ በሰላም ነው ያለው።
run_women2
run_women1
ከመነሻው የእህቶቻችንን የነጻነት ድምጽ እያዳመጡ ሲክታተሏቸው የነበሩት የደህንነት ኃይሎች ሩጫውን እንዳለቀ በርካታ ሴቶችን አፍሰው ወደ ሾላ የካ ፖሊሰ መምሪያ ወህኒ ቤት ይወስዷቸዋል። ወንጀላቸው ምንድን ነው ? በአገራቸው ድምጻቸው ከፍ አደርገዉ የነጻነትን ድምጽ ማሰማታቸው።
ከታሳሪዎቹ መካከል ሁለቱ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ሲሆን ሌሎች ደግሞ የሰማያዊ አባላትና ደጋፊዎች ናቸው። ከሴትቹ ጋር አብረው የነበሩ ፣ ሴቶች ታፍሰው ሲወሰዱ ለምንድን ነው የምትወስዷቸው ያሉ ወንዶችም፣ «ለምን? » ብለው በመጠየቃቸውም አብረው ለእስር ተዳርገዋል።
መጋቢት 1 ቀን 2006 ዓ.ም፡
እስረኞቹ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። መርማሪዎ ፖሊስ ኮማንደ ርየማታ ይባላሉ። « የተከሰሱበት ምክንያት እሁድ የካቲት 30 ቀን በተካሄደው የሴቶች ሩጫ ላይ ተመሳስሎ በመግባት፣ “የጣይቱ ልጆች ነን ፣ የምኒልክ ልጆች ነን ፣ ኑሮ መረረን ፣ የህሊና እስረኞች ይፈቱ” በሚል ሁከትን ለማነሳሳት ቀስቅሰዋል። መረጃ አሰባስቤ ስላልጨረስኩ፣ መረጃዎቼን እንዳያጠፉብኝ፣ ሰዎችም እንዳይመሰክሩ እንዳያስፈራሩ፣ በተጨማሪም ብዙዎቹ ቋሚ አድራሻ የሌላቸው ስለሆነ፣ መረጃ እስካሰባስብ የ15 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ» ይላል። ፍርድ ቤቱ ግን «አራት ቀን ይበቃቹሃል» በማለት ለመጋቢት 5 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጣል።
መጋቢት 5 ቀን 2006 ዓ.ም፡ 
የሰማያዊ ወጣቶች የፍርድ ቤት ውሎ (ዳዊት ሰለሞን እንደዘገበው)
ባሳለፍነው ሳምንት ታላቁ ሩጫ ባዘጋጀው የሴቶች ውድድር ላይ በመሳተፍ ተቃውሞ በማሰማታቸው ለእስር የተዳረጉት ሰባት ሴቶችና ተባባሪ ተደርገው የታሰሩ ሶስት ወንዶች ዛሬ በነበራቸው ቀጠሮ መሰረት ቀበና በሚገኘው ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር፡፡
ታሳሪዎቹ በአንድ ፖሊስ ጣብያ ውስጥ የከረሙ ቢሆንም ፖሊስ ወደ ፍርድ ቤቱ በመጀመሪያ ያመጣው ወንዶቹን ነበር፡፡ሴቶቹ ለሰዓታት ዘግይተው በሩጫው ወቅት ለብሰውት የነበረውን ባለ ሙሉ ቢጫ ቀለም ቲ ሸርት እንደለበሱ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡
ዳኛው ከተሰየሙ በኋላ ከሳሽን በመወከል የቀረቡ ሁለት ፖሊሶች ‹‹ምርመራችንን ባለማጠናቀቃችን ተጨማሪ የሰባት ቀን የምርመራ ግዜ ይፈቀድልን››በማለት ጠይቀዋል፡፡የተከሳሾች ጠበቃ(የጋዜጠኛ ርዕዮት ወላጅ አባት አቶ አለሙ ጎቤቦ) ፖሊስ ደምበኞቼን በእስር ለማቆየት ካለው ፍላጎት እንጂ ወንጀሉ ተፈጸመ የተባለው በአደባባይ በመሆኑ ተጨማሪ ምርመራ አያስፈልገውም ስለዚህ ደምበኞቼ ጉዳያቸውን በውጪ ሆነው እንዲከራከሩ ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸውን ያክብርልኝ››በማለት ተከራክረዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የመናገር እድል እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ሲፈቀድላቸው ‹‹ሲቪል የለበሱ ሰዎች እየመጡ በሌሊት ጭምር ከታሰሩበት ቤት እንዲወጡ በማድረግ እንገድላችኋለን፣ከአሸባሪዎች ጋር መስራታችሁን አቁማችሁ አብራችሁን ስሩ፣በመጥረጊያ አናትሽን ብልሽ የሚደርስልሽ አይኖርም››የሚሉ ማስፈራሪያዎችን እንዳደረሱባቸው በመግለጽ ዋስትና ይሰጠን ሲሉ አቤት ብለዋል፡፡
ፖሊሶቹ በተከሳሾች የቀረበው ሐሰት መሆኑን በመግለጽ ‹‹ሴቶቹ ለምሳሌ ወደዚህ ለመምጣት የቆዮት የለበሱትን ቲሸርት እንዲለውጡ ሲነገራቸው እምቢ በማለታቸው ነው፡፡በመኪና ላይ ይጨፍሩ ነበር፡፡እስር ቤት ውስጥም ሌሎች እስረኞችን ያነሳሳሉ ››ብለዋል፡፡
ቲሸርቱ በፍርድ ቤት እንዳይለበስ ያልታገደ በመሆኑ መልበስ መብታቸው ነው ያሉት አቶ አለሙ ‹‹ደምበኞቼን ፖሊስ በፈለገው ጊዜ ሊያገኛቸው የሚችል በመሆኑ በእስር መቆየታቸው ተገቢ አይደለም››ብለዋል፡፡
የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጡት ዳኛው ‹‹ፖሊስ የእስረኞቹን መብት ማክበር ግዴታው ነው ስለዚህ የተባለው ነገር እንዳይደገም በማለት የዋስትና መብታቸውን ሳይጠብቁ ለፖሊስ ተጨማሪ አራት ቀን በመፍቀድ ተጠርጣሪዎቹ ወደ ፖሊስ ጣብያ እንዲመለሱ አዘዋል፡፡
እስረኞቹ በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ችሎት ቢቀርቡም ፖሊስ አሁንም ‹‹ምርምራውን አልጨረስኩም፣ ተጨማሪ የምይዛቸው ሰዎች አሉ፣ የተያዙትም ቢለቀቁ ሌላ ወንጀል ይሰራሉ›› በሚል ሰባት ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጡት ይጠይቃል።
በአንጻሩ የታሳሪዎቹ ጠበቃ ሆነው የቀረቡት የጋዜጠኛ ርዕት አለሙ አባት አቶ አለሙ ጌደቦ በበኩላቸው ፖሊስ ተሰጥቶት የነበሩት ሰባት ቀናት መረጃ ለማሰባሰብም ሆነ ሌሎች የምይዛቸው ተጨማሪ ሰዎች አሉ ያላቸውን ቢኖሩ ኖሮ ለመያዝ በቂ እንደነበር አያስረዳሉ፡፡ በተጨማሪም ታሳሪዎቹ በኃላፊነት ቦታ ላይ የሚሰሩና ቋሚ አድራሻ ያላቸው በመሆኑ በዋስ ተለቀው ጉዳያቸውን መከታተል ስለሚችሉ የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ይከርከራሉ።
ፍርድ ቤቱ እንደገና ለስረኞች የዋስትና መብት ከልክሎ መጋቢት 9 ቀን ፖሊስ ሁኡን ናገር አጠናኽሮ እንዲቀርብ ያዛል። እንደገና ተጨማሪ አራት ቀናት ለፖልሲ ተሰጠ።
መጋቢት 9 ቀን 2006 ዓ.ም
እስረኞች እንደገና ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። ፖሊስ ምንም መከራከሪያ ማቅረብ አልቻለም። እንደገና 14 ቀናት ይስጠኝ ብሎ ይጠይቃል። በፍር ድቤቱ ቁጥሩ እጅግ በርካታ ሰው አለ። መቀመጫዎቹ ሁሉ ሞልተው የቆሙ ብዙ ናቸዉ። በዉጭም በብዛት አሉ። የተለያዩ ዬምባሲ ተወካዮች፣ ጋዜጠኞችም የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት በቦታው አሉ። እስረኞቹ መጋቢት 1፣ መጋቢት 5 ቀን ቀርበው ፣ ፖሊስ ዝግጁ አይደለሁም በሚል ለመጋቢት 9 ተላልፎ ነበር። በመጋቢት 9 ፖሊሲ ስራዉን አጠናቆ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ መመሪያ ሰጥቶ ነበር። ነገር ግን መጋቢት 9 ቀን፣ አሁንም ፍርድ ቤቱ ሌላ ሰበብ በመስጠት ቀኑን አራዘመ። ጉዳዩ በመደበኛ ፍርድ ቤት እንዲታይ ሲል ቀጠሮዉን ለነገ መጋቢት 10 ቀን 2006 ዓ.ም አስተላለፈ።
የነገዉን የፍርድ ቤቱ ዉሎ ዘገባው እንደደረሰን የምናቀርብ መሆናችንን ለማሳወቅ እንወዳለን።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar