fredag 7. mars 2014

አንድነት ፓርቲ ሁለተኛውን ዙር “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” ህዝባዊ ንቅናቄ ይፋ አደረገ!!

ህዝባዊ ንቅናቄው የሚካሄድባቸው 17 ከተሞችም ተለይተው ታውቀዋል፤
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዛሬ ይፋ ያደረገው የህዝባዊ ንቅናቄ መርሃ ግብር በተከታታይ ሊካሂዳባቸው ካቀዳቸው ህዝባዊ ንቅናቄዎች መካከል አንዱ የሆነውን “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባቤትነት”(Millions of voices for land ownership) የሚል ስያሜ የሰጠውን የህዝባዊ ንቅናቄ ነው፡፡ መረሃ ግብሩ በዛሬው እለት ይፋ የተደረገው ቀበና መድኃኔዓለም ቤ/ክ ፊት ለፊት በሚገኘው የፓርቲው ጽ/ቤት ነው፡፡ ህዝባዊ ንቅናቄው ይፋ በተደረገበት መግለጫ ላይ አንድነት የመሬትን ጉዳይ በአጀንዳነት በመምረጥ ህዝባዊ ንቅናቄ ለማድረግ የመረጠባቸው ምክንያቶች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡
በአዲስ አበባ በሚደረግ ትዕይንተ ህዝብ እንደሚጀመር የሚጠበቀው “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባቤትነት” ህዝባዊ ንቅናቅ 14 ከተሞች ላይ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግና ሶስት ከተሞችም በተጓዳኝ ለህዝባዊ ንቅናቄው መመረጣቸው ታውቋል፡፡ ንቅናቄው የሚካሄድባቸው ከተሞች አዲስ አበባ፣ ደሴ፣ አዋሳ፣ አዳማ/ናዝሬት፣ መቀሌ፣ ደብረታቦር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ድሬ ደዋ፣ ጅንካ፣ ቁጫ፣ አሶሳ፣ ነቀምት፣ ለገጣፎ፣ አዲስ አበባ ሲሆኑ ተጓዳኝ ከተሞቹ ወልዲያ፣ ጋምቤላ፣ ም/አርማጨሆ(አብርሃ ጅራ) እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡
አንድነት ፓርቲ ባለፈው ዓመት(2005ዓ.ም) ለሶስት ወራት “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል ስክታማ ህዝባዊ ንቅናቄ ማድረጉ ይታወሳል፡፡993754_546619252089680_666940779_n

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar