torsdag 27. mars 2014

የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ቀጣይ የተቃውሞ መርሃግብር




ላለፉት 2 አመታት ሲካሄድ የቆየው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጋብ ብሎ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አርብ እንደሚጀመር ታውቋል። የተቃውሞ መሪ መፈክሩ “ሰላታችንን በመስኪዳችን” የሚል እንደሆነና መስኪዶችን በመንግስት ታማኞች ለማስያዝ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመቃወም አላማ ያደረገ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የፍርድ ሂደት ዛሬ ተጀምሯል። ተከሳሾቹ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ለማሰማት በተገኙበት ወቅት የማህልና የቀኝ ዳኞች ተቀይረው በአዲስ ተተክተው አግኝተዋቸዋል።
የአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የሚካሄደው የፍርድ ሂደት ፖለቲካዊ ይዘት ያለውና ነጻ አይደለም በማለት ውድቅ ማድረጋቸው ይታወቃል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar