torsdag 6. mars 2014

ሰበር ዜና የኦሮሞያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ትናንት ሌሊትአረፉ



የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንትነቱን ስልጣን ሳያስረክቡ እንዳስረከቡ ተደርጎ የተነጠቁት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ታይላንድ ባንኮክ ውስጥ በጥብቅ የህክምና ክትትል ወይም (ኢንቴንሲቭ ኬር ዩኒት) ውስጥ እንደሚገኙ ኢሳት አረጋግጧል።
ግለሰቡ ያለመሳሪያ ድጋፍ በራሳቸው መተንፈስ እንደማይችሉ ፣ ሰዎችን እንደማያናግሩና በዶክተሮች ከፍተኛ ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኙ እኩለቀን ላይ አንድ የሆስቲታሉ ሰራተኛ ለኢሳት ተናግረዋል።
አቶ አለማየሁ ከኦህዴድ የምክር ቤት አባላት ጋር በክልሉ ስለሚታየው ሙስናና የመልካም አስተዳደር መበላሸት ጭቅጭቅ የተሞላበት ስብሰባ ካደረጉ በሁዋላ ወንበራቸው ላይ እንደተቀመጡ ራሳቸውን መሳታቸው ይታወቃል።
በወቅቱ አብረዋቸው የነበሩት አዲሷ የኦህዴድ ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ አስቴር ማሞ አቶ አለማየሁ ገርጂ በሚገኝ ሆስፒታል አስቸኳይ ህክምና እንዲያገኙ ከተደረገ በሁዋላ ሆስፒታሉ ወደ ውች እንዲላኩ ማዘዙንና ማምሻውን ወደ ውጭ እንዲላኩ ተደርጓል። ባንኮክ ከደረሱበት እለት ጀምሮ አቶ አለማየሁ ራሳቸውን በመሳት ሰዎችን ለማነጋገር ሳይችሉ ቀርተዋል። ባለቤታቸው ከጎናቸው በመሆን እያስታመሙዋቸው መሆኑንም ኢሳት ለመረዳት ችሎአል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar