tirsdag 18. mars 2014

በኑሮ ዉድነት ላይ በአዲስ አበባ የአንድነት ምክር ቤት ሰልፍ ሊጠራ ነው !


የአንድት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ስራ አስፈፃሚ የተቃውሞ ሰልፍ ሊጠራ ነው እንደሆነ የፍኖት ጋዜጣ ዘገበ። «በአዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የውሃ፣የመብራትና የቴሌኮም አገልግሎት ጥራት መጓደልና የአገልግሎት መቋረጥ መንግስት በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ለመጠየቅ፣ የከተማዋን ነዋሪዎች በማነቃነቅ ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የአንድት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ስራ አስፈፃሚ መወሰኑን የዞኑ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ» ሲል ነው ፍኖት የዘገበው።
ይህ የአንድነት ፓርቲ አዲስ አበባ ምክር ቤት የሚጠራዉ ሰልፍ፣ የአንድነት ፓርቲ ይፋ ካደረገው የአሥራ አራት ከተሞች የሚሊየንም እንቅስቃሴ የተለየና በተጨማሪ የሚደረግ ሲሆን፣ የሚሊየነም እንቅስቃሴ በመሬት ባለቤትነትና በፍትህ ላይ ያተኮረ እንደሆነ በስፋት የተዘገበ ነው።
የአዲስ አባበ የአንድነት ምክር ቤት፣ በሃያ ሶስቱም የአዲስ አበባ ወረዳዎች መቃቅር ያለው ሲሆን፣ ከማእከላዊ ፓርቲ ዉጭ፣ በራሱ በርካታ እንቅስቃሴዎች የሚያደርግ ምክር ቤት እንደሆነ ይታወቃል። ፓርቲዉ አባላትን በአዲስ አበባ እንዳደረጉት በራሳቸው አነሳሽነት ሰላማዊን ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች እንዲያደርጉ የሚያበረታታ እንደሆነ ብዙ ጊዜ አመራር አባላቱ ሲናገሩ ተሰምተዋል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar