tirsdag 1. oktober 2013

አንድነት ፓርቲ የእሁዱን ሰልፍ ውጤት እየገመገመ ነው

የፓርቲው አመራሮች በዛሬው እለት ተሰብስበው ትናንት እሁድ ፓርቲው የጠራውን ሰለማዊ ሰልፍ ውጤት ገምግመዋል። መስቀል አደባባይ ብንሄድ ኖሮ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ሊገኝ እንደሚችል የተናገሩት አቶ ደንኤል፣ በከፍተኛ አፈና ውስጥ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ከ80 ሺ በላይ በሆነ ህዝብ መካሄዱ የተሳካና ለሚቀጥለው ሰልፍ ፍንጭ የሰጠ፣ ህዝቡ ለውጥ ፈላጊ መሆኑንና ከፓርቲያቸው ጎን የቆመ መሆኑን ለማየት ችለናል ብለዋል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ ሽመልስ ከማል በበኩላቸው  በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው ፍርድ ያገኙና ፍርድ ለማግኘት የሚጠባባቁትን በአደባባይ መደገፍ የሚያስጠይቅ ወንጀል መሆኑን ጠቅሰው፣ የሚያመጣውን መዘዝ ለመቀበል ፓርቲ ዝግጁ መሆን አለበት ብለዋል።
አቶ ሽመልስ ከማል የሰጡት መልስ አሳፋሪ ነበር ያሉት አቶ ዳንኤል፣ ከመንግስታቸው ጋር ተማክረው ያደረጉት አይመስለኝም ሲሉ አክለዋል።
አቶ ዳንኤል የኢቲቪን ዘገባም እጅግ አሳፋሪ ነበር ሲሉ አጣጥለውታል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar