tirsdag 29. oktober 2013

ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞቹን አባረረ

 
የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች ባለፈው ነሀሴ ወር ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ በፋብሪካው አስተዳደር ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገልፀው ነበር፡፡ ቦርዱ እና ማነጅመንቱ ሰራተኞቹን በመሰብሰብ መልስ እንደሚሠጡ ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም፣ ቃላቸውን በማጠፍ  በጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም ሰራተኞቹን ለአመፅ አነሳስተዋል ተብለው የተፈረጁ 27 ሰራተኞች ከስራ አባረዋል ፡፡ በእለቱ የወጣው የማገጃ ደብዳቤ በፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ አባይ መላኩ ፊርማ የተጻፈ ነው።
የፋብሪካው ስራስኪያጅ ሰራተኞች መባረራቸውን አምነው ቁጥራቸው ግን 5 ብቻ ብለዋል፡፡ ስራ አስኪያጁ ሰራተኞቹ የተባረሩት  ምንም እውቅና የሌለው ህገ ወጥ የስራ ማቆም አድማ ስላደራጁ ነው ብለዋል

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar