mandag 7. oktober 2013

በአፋር የክልል የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ በወታደራዊ ካምፕ ውስጥ እየተካሄደ ነው

ካለፉት 3 አመታት ጀምሮ በክልሉ ከመልካም አስተዳደር እና ከሰዎች መፈናቀል ጋር በተያያዘ የሚታየው ችግር እየተባባሰ በሚገኝበት ሁኔታ የክልሉን ባለስልጣናት ለመምረጥ በአዋሽ አርባ ታንከኛ ማሰልጠኛ ግቢ ውስጥ ስብሰባ እየተካሄ ነው።
ከፍተኛ የህወሀት ድጋፍ አላቸው የሚባሉት የአቶ እስማኤል አሊሴሮ ደጋፊዎች በአንድ በኩል ፕሬዚዳንቱን የሚቃወሙ ሰዎች በሌላ በኩል ሆነው በስብሰባው ላይ የተገኙ ሲሆን ፣ ፕሬዚዳንቱና ደጋፊዎቻቸው እራሳቸው  ተመራጭና አስመራጭ በመሆን ስብሰባውን እየመሩት ነው።
ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ በመቀመጥ የሚታወቁት የአንደኛ ደረጃ ተማሪው አቶ እስማኤል፣ አቶ ስዩም አወልን፣ አቶ ሙሀመድ አምበጣ፣ አቶ አወል ወቲካን እና አቶ አወል ማሊን ከጎን በማሰልፍ የምርጫውን  ውጤት ለመቆጣጠር ሙከራ አድርገዋል።
በአፋር ክልል ባለስልጣናት መካከል የተፈጠረውን የስልጣን ሽኩቻ መዘገባችን ይታወቃል። ፕሬዚዳንት አሊ ሴሮ አሸንፈው ለሚቀጥሉት 5 አመታት በስልጣን ላይ የሚቆዩ ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ የቆዩ የክልል መሪ ይሆናሉ።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar