onsdag 30. oktober 2013

በምሥራቅ ጎጃም የሚገኘው የዳገት እየሱስ ቤተክርስቲያን ባልታወቁ ሰዎች የቃጠሎ አደጋ ደርሶበታል



በምሥራቅ ጎጃም የሚገኘው የዳገት እየሱስ ቤተክርስቲያን ባልታወቁ ሰዎች የቃጠሎ አደጋ ደርሶበታል፥ ባለፉት ጥቂት ወራቶች ውስጥ በዚሁ መምሥራቅ ጎጃም ሃገረ ስብከት ውስጥ በጠቅላላው ወደ 4 የሚጠጉ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት የቃጠሎ አደጋ እንደደረሰባቸው ከሥፍራው የደረሰን ሪፖርት ያሳያል።
በሃገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ቤተክርስቲያናት፣ አድባራት፣ ገዳማት እንዲሁም የአብነት ትምህርት ቤቶች ባለፉት 20 ዓመታት ሲቃጠሉ፣ ሲወድሙ ተመልክተናል ነገር ግን ቤተክህነቱ ምንም ሊያደርግ አልቻለም ወይንም የእምነቱ ተከታዮች ምንም ማድረግ አልቻሉም ወይንም አይመለከተንም ብለው ተቀምጠዋል። በጣም በእጅጉ የሚያስፈራው በቀጣይነት ክርስቲያኖች በየቦታቸው እየታደኒ አደጋ እንዳይደርስባቸው ስጋት አለን። እግዚአብሔር ይሁነን
የወያኔውች ስራ ነው ይሄን ቦታ ሊያስለቅቋቸው መሆን አለበት እንጂ እንዴት ይሄ ሁሉ ቤተክርስቲያን አንድ ዓመት ያውም አራት ወር ባልሞላግዜ ውስጥ ይቃጠላል?አገር አስተዳድራለሁ የሚለው መንግስት ተብየው እንዴት ዝም አለ?እጁ ቢኖርበትም አይደል?
ቤተክርስቲያንንና ገዳማትን ከጥቃት ለመከላከልና የፈረሱትንና የተቃጠሉትን ለመስራት የበኩሉዎን አስተዋፆ ያደርጉዘንድ ይለመናሉ::

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar