tirsdag 29. oktober 2013

በአንድነት ፓርቲ በሰላማዊ ትግል ላይ እየተሰጠ ያለው ስልጠና በስኬት እንደቀጠለ ነው


በአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ክፍል የተዘጋጀውና በሰላማዊ ትግል ላይ ሰፊ ምርምር ባደረጉት በአቶ ግርማ ሞገስ በሰላማዊ ትግል ላይ እየተሰጠ ያለው ሳምንታዊ ስልጠና ቀጥሏል፡፡ በስልጠናው በሰላማዊ እና ትጥቅ ትግሎች መካከል ንጽጽራዊ ትንተና የተሰጠ ሲሆን ትንተናው በስድስት ክፍሎች የተከፋፈለ ነበር፡፡
የሰላማዊ ትግል እና የትጥቅ ትግል ልዩነቶች በመንግስት የፖለቲካ ኃይል ምንጮች (የስልጣን ምንጮች) ጥያቄ ዙሪያ፣ መንግስት በማስወገድ ጥያቄ ዙሪያ፣በመዓከል አመራረጥ ጥያቄ ዙሪያ፣በአደረጃጀት ጥያቄ ዙሪያ፣በስትራተጂያዊ ዘመቻዎች ጥያቄ 

ዙሪያ፣ትግሎቻቸውን በሚያራምዱባቸው መሳሪያዎች ጥያቄ ዙሪያ፣በመንግስት አመሰራረት ጥያቄ ዙሪያ፣በሞራል ጥያቄ ላይ ያላቸው ተቃርኖ፣ በፖለቲካ ባህል ጥያቄ ላይ ያላቸው ተቃርኖ፣በሰበኣዊ መብት ማክበር ጥያቄ ላይ ያላቸው ተቃርኖ፣ህዝብን በማቀራረብ፣ በማግባባት እና በአስታራቂነት ጥያቄ ላይ ያላቸው ተቃርኖ፣ህዝብን የራሱ ነፃ አውጪ በማድረግ ጥያቄ ላይ ያላቸው ተቃርኖ፣በዴሞክራሲ ሽግግር ጥያቄ ላይ ያላቸው አስተዋጽኦ ተቃርኖ እና ከአገር ጠላት አገሮች ጋር በመወዳጀት እና የአገር ሉዓላዊነትን በማስደፈር ጥያቄ ላይ ያላቸው ተቃርኖ በሰፊው ተብራርቷል፡፡
በስልጠናው ሰላማዊ ትግል እና ትጥቅ ትግል ተጋጋዥ ናቸው የሚለው አባባል ትክክል ነውን? የሚለው ነጥብ ሰፊ ትንተና ተሰጥቶበታል፡፡

የ“ሁለገብ የትግል ዘዴ” ማለት ምን ማለት ነው? ማድረግ ይቻላልን? በሚለውነጥብ ላይ ሰፊ ትንተና የተሰጠ ሲሆን ሁለቱን የትግል ስልቶች በጋራ መጠቀም እንደማይቻልና እጅግ ተፃራሪ መሆናቸውን አቶግርማ አብራርተዋል፡፡
ትጥቅ ትግል የመሳሪያ ቀላዋጭ እና የአገር ከሃዲ ያደርጋል፣ የአገር አንድነት ያናጋል፣ የአገር መፍረስ ያስከትላል፣ ሉዓላዊነትን ያስደፍራል፣ ከኢትዮጵያ ጠላት ጋር ያሻርካል። ከታሪካችን የተለቀሙ መረጃዎች፥ በማሰባሰብም
በአፄ ቴዎድሮስ ዘመን የተፈጸመ፣ ከ አፄ ቴዎድሮስ በኋላ እስከ ምኒልክ ዘመን የተፈጸሙ፣ በደርግ ዘመን የተፈጸሙ እንዲሁም ዛሬ ከኢሳያስ ጋር በመፈጸም ላይ የሚገኙ ስህተቶችን ተንትነዋል፡፡
በመጨረሻም በስልጠናው ሀሳብ ላይ መደምደሚያ ከተሰጠ በኋላ የስልጠናው ተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችን አንስተው በአቶ ግርማ ሞገስ ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ስልጠናው በመጪው ቅሜም እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡ ስልጠናው በቃሌ ፓልቶክ ሩም ውስጥም በቀጥታ ተላልፏል፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar