torsdag 3. oktober 2013

በባህርዳር ድሆች መኖሪያ ቤታቸውን እየተቀሙ ለጎዳና ተዳዳሪነት ተዳርገዋል

የድሃ ድሃ ተብለው ተመርጠው ኑሮቸውን በጉስቁልና የሚመሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከደርግ ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድርስ በቀበሌ ቤቶች ሲገለገሉ ቢቆይም ያለ አግባብ በባለስልጣናት እየተቀሙ መሆኑ ለከፍተኛ ችግር እንዲጋለጡ እንዳደረጋቸው ነዋሪዎቹ ለኢሳት ገልጸዋል።
የመንግስት ባለስልጣናት ደሀዎችን “ተተኪ ቦታና ቤት ይሰጣችሁዋል” በማለት ቤቶችን እየቀሙ ለባለሐብቶች እና ለራሳቸው በሊዝ እየገዙ አዳዲስ ህንጻዎችን መገንባታቸውን ተከትሎ ድሆች ጎዳና ላይ እንዲወድቁ ግድ እንዳለ ያነጋገርናቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ገልጸዋል።
ችግሩ እንዲፈታላቸው ለመንግስት አካላት ለአመታት አቤት ቢሉም ምንም መፍትሄ እንደላገኙ ይናገራሉ። አንዳንዶች ቤታቸው ከፈረሰባቸውና ጎዳና ላይ ማደረግ ከጀመሩ 5 አመታት አልፎአቸዋል፤ ካሳ ወይም ተተኪ ቤት አለማግኘታቸውን በምሬት ይገልጻሉ።
በመላ አገሪቱ ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው ለጎዳና ተዳዳሪነት የተዳረጉ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar